Remove the sign of star from an Ethiopian flag
Firew Lemma 0

Remove the sign of star from an Ethiopian flag

Show your support by signing this petition now
Firew Lemma 0 Comments
3 people have signed. Add your voice!
1%
Maxine K. signed just now
Adam B. signed just now

የኢትዮጵያ ባንዲራ ላይ የሚገኘዉ የኮከብ ምልክት ይነሳልን

ለኢፌድሪ ፕሬዚደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ

ለኢፌድሪ ጠቅላይ ሚንስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ

ለኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስቴር አቶ ደመቀ መኮንን

ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሙፈሪያት ከማል

የተከበራችሁ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት

የተከበሩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ያለዉ አባተ

የተከበራችሁ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት

የተከበራችሁ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች

የተከበራችሁ የክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎችና የምክር ቤት አባላት

የተከበራችሁ የዞን/ ልዩ ወረዳ/ የወረዳ አስተዳዳሪዎች

የተከበራችሁ የዞን/የልዩ ወረዳ/ እና የወረዳ ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎችና የምክር ቤት አባላት

የተከበሩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ

የተከበሩ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ምክር ቤት አፈጉባኤና የምክር ቤት አባላት

የተከበራችሁ የከተማ መስተዳድር ከንቲባዎች

የተከበራችሁ የከተማ መስተዳድር አፈ ጉባኤዎችና የምክር ቤት አባላት


እንደሚታወቀዉ ሀገራችን ኢትዮጵያ የነጻና የኩሩ ህዝቦች መኖሪያ፣ በልጆቿ ታፍራና ተከብራ የኖረች፤ ለጥቁር ሕዝቦች ሁሉ የክብር፣ የነጻነት እና የሥልጣኔ ተምሳሌት በመሆን በአለማችን ላይ ብዙ ሁነቶች ሲቀያየሩ እስከዛሬ ድረስ ጸንታ የቆመች ቀደምት ሀገር ናት፡፡

ታዲያ ይህች ሀገር በብዙ ዉጣ ዉረድ ዉስጥ ብታልፍም እስከዛሬ ድረስ አብሯት የዘለቀ፤ ክቡር ልጆቿ አጥንታቸዉን ለመከስከስ እና ደማቸዉን ለማፍሰስ ያልሳሱለት፣ ሁሉም ህዝቦቿ በእኩልነት የህይወት መስዋዕትነት በመክፈል ጠብቀዉ እንዲያቆዩዋት ትልቁን አስተዋጽኦ ያበረከተዉ ባለ አረንጋዴቢጫ እና ቀይ ቀለማቱ የሰንደቅ አላማችን መሆኑ ይታወቃል፡፡

ምንም እንኳን የመንግስታትን መቀያየር ተከትሎ በባንዲራችን ላይ የራሳቸዉን አርማ ያስቀመጡ ነገስታት ቢኖሩም፤ ባለ 3 ቀለማቱ (አረንጋዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ) ባንዲራችን ግን ዘር፣ ብሔር እና ሀይማኖት ሳይለይ እስከዛሬ ድረስ ሳይቀየር ህዝባችንን አንድ አድርጎ በማስተሳሰር ቆይቷል፡፡

የቅርብ ጊዜ ታሪካችን በሆነዉ የደርግ ዘመነ መንግስት ባንዲራችን(አረንጋዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ)፤ የማንንም ፍላጎት፣ እምነት ወይንም ደግሞ ርዕዮተ ዓለም የሚያንጸባርቅ ምልክት ያልተለጠፈበትን፤ ንጹሁን ባንዲራችንን የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ ልቡ ተቀብሎት፣ ለዚህ ባንዲራ ሲል ክቡር ህይወቱን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች መስዋዕት አድርጓል፡፡

ነገርግን ክቡርነትዎ እርስዎም እንደሚያዉቁት በጥቅምት 21/ 1989 ዓ.ም በባንዲራችን ላይ የተለጠፈዉ መደቡ ሰማያዊ ሆኖ፤ ባለ ቢጫ ቀለሙ አምስት ጫፍ ያለዉ ኮከብ እና አምስት የጨረር ፍንጣቂዎች ምልክት፤ ከኢትዮጵያ ህዝቦች መልካም ይሁንታ እና በጎ ፈቃድ ዉጪ የተደረገ በመሆኑ፤ ምንም እንኳን ከዚህ ባንዲራ ዉጪ ይዞ መገኘት በአንድ አመት እስራት እና የ5000.00/የአምስት ሺህ ብር/ የገንዘብ ቅጣት የሚያስቀጣ ቢሆንም፤ ኢትዮጵያዉያን ግን በነጻነት ሃሳባቸዉን ለመግለጽ እድሉን ባገኙበት አጋጣሚ ሁሉ የሚደርስባቸዉን ቅጣት ሳይፈሩ፤ ለምሳሌ ያህል ህዝብ በብዛት በሚሳተፍባቸዉ ስብሰባዎች፣ ሕዝባዊ በዓላት፣ ስፖርታዊ ዉድድሮች፣ የሙዚቃ ኮንሰርቶች እና የመሳሰሉት ላይ ንጹሑን ባንዲራ ይዘዉ ሲወጡ መመልከት የተለመደ ነዉ፡፡

እኛ አትዮጵያዉያን ጨዋ ህዝቦች እና ህግ አክባሪ ዜጎች ስለሆንን በምንም መልኩ የህግ ተላላፊዎችን አንደግፍም ወይንም ደግሞ አናበረታታም፡፡ ነገርግን እርስዎም ወደ ሕዝብ መሪነት ከመጡም በኋላ እንኳን በስንት ትግል ያስፈቷቸዉን ዉድ የኢትዮጵያ ልጆችን ምልክት የሌለበትን ባንዲራ ይዛችኋል በማለት እንዳሰሯቸዉና፤ በእርስዎና በኢትዮጵያ ህዝብ ትግል እንደተፈቱ ያስታዉሳሉ፡፡

አሁን ግን ፈጣሪ የኢትዮጵያን ህዝብ ልመና ሰምቶ በእኩልነት ህዝቦቹን የሚመለከት እና የሚወድ መሪ ስለሰጠን፤ በትህትና እና በታላቅ አክብሮት የምንጠይቅዎት ይህንን ኩሩና ዉብ ሕዝብ የማይወክለዉን ምልክት ከባንዲራችን ላይ በማንሳት፣ በዚህች ጥቂት የስልጣን ጊዜዎ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይመለሱለታል ተብለዉ ፈጽመዉ የማይታሰቡ ብዙ መብቶቻችንን መልሰዉ እንዳጎናጸፉን፣ ኢትዮጵያዊነት ክብራችንን፣ የሀገር እና የሥልጣን ባለቤትነታችንን እንዳስመለሱልን ሁሉ፤

ባንዲራችንንም አስመልሰዉልን አንገታችንን ቀና አድርገን በኢትዮጵያዊነታችን ዳግም እንድንኮራ ያደርጉን ዘንድ በትልቅ አትዮጵያዊ ትህትና እና አክብሮት እንጠይቆታለን፡፡

ኢትዮጵያ በልጆቸ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር፡፡

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ዝቦቸን ለዘላለም ይባርክ!፡፡

Share for Success

Comment

3

Signatures