የኢትዮጵያ ገዳማት ህልውና ይከበር!
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታላላቅ እና ታሪካዊ ገዳማት አንዱ ነው፤ ለግሑሳን(ፍጹማን) ባሕታውያን መሸሸጊያ፣ ለስውራን ቅዱሳን መናኸርያ፣ በብዙ ሺሕ ለሚቆጠሩ መነኮሳት፣ መነኮሳይያት እና መናንያን መጠጊያ፣ ለምእመናኑንም መማፀኛ እና ተስፋ ነው - የዋልድባ ገዳም፡፡
ቅዱሳን አበው እንደ ጽፍቀተ ሮማን የሰፈሩበት፣ እንደ ምንጭ የሚፈልቁበት ገዳሙ እመቤታችን ከልጇ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መዋዕለ ስደት ወቅት በኪደቱ እግር ከረገጧቸው መካናት አንዱ ነው፡፡ በወቅቱ ጌታችን
የወይራ ተክል ተክሎና አለምልሞ አርኣያ ስቅለቱን ገልጾበታል፤ ለቅዱሳኑ “እንደ ኢየሩሳሌም ትኹንላችሁ፤” ብሎ ቃል ኪዳን
በመስጠት እህል እንዳይዘራባት፣ ኀጢአት እንዳይሻገርባት፣ ከድንግል አፈሯ የተቀበረ እንዳይወቀስባት እንዳይከሰስባት
አዝዟል፡፡ በሰሜን ተራራዎች ግርጌ ዙሪያዋን በሰሜን አንሴሞ፣ በምሥራቅ ተከዜ፣ በምዕራብ ዘወረግ እና በደቡብ ዜዋ
በተባሉ አራት ወንዞች በተከበበችውና የኢትዮጵያ ገዳማት ሁሉ መመኪያ በተባለችው ገዳም ከሙዝ ተክል ከሚዘጋጀው
ቋርፍ እና ቅጠላ ቅጠል በቀር እህል አይበላባትም፡፡
በዚያ ቅዱሳን አበው፣ መነኮሳት እና መነኮሳይያት ረሀቡንና ጥሙን ታግሠው፣ የአገርን ቅርስና ሀብት ጠብቀው ለኢትዮጵያና ለመላው ዓለም እያለቀሱና እየጸለዩ፣ ዲማ በተባለው ፍልፍል ዛፍ በኣታቸው እያለፉ ኖረዋል፤ ቦታው ከፍተኛ የድኅነትና ሃይማኖት ሥፍራ ነውና ዛሬም ለአገር ሰላም፣ ፍቅርና ዕድገት ያልተቋረጠ ጸሎት እየተካሄደበት የሚገኝበት ቢሆንም ለ2000 ዓመታት በነገሥታቱ ሳይቀር ተጠብቆ የኖረውን ክብሩንና ሞጎሱን የሚፈታተን፣ ገዳማዊ ሕጉንና ሥርዐቱን የሚጋፋ፣ ማኅበረ መነኮሳቱንም ለከባድ ኀዘንና ጭንቀት የሚዳርግ አደጋ ተጋርጦበታል፡፡
የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ዘቤተ ሚናስ ማኅበር፣ የዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳም ማኅበር እና የዋልድባ
ዳልሽሓ ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም ማኅበር ምልአተ ጉባኤ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ መለስ ዜናዊ በጻፉት አምስት ገጽ
ደብዳቤ ላይ እንደተገለጸው፤ በዓዲ አርቃይ ወረዳ በኩል የዋልድባን ገዳም ውስጡን በፓርክነት ለመከላከል በቀለም የተቀለሙ ምልክቶች እየተተደረጉ ነው፡፡ በወልቃይት ወረዳ ልዩ ስሙ መዘጋ በተባለ የገዳሙ የእርሻ እና አዝመራ ቦታ ላይ
መንግሥት የዛሬማን ወንዝ ገድቦ የስኳር ፋብሪካ ለማቋቋም በሰፊው እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ በገዳሙ ክልል ዘልቆ
የሚያልፍ ጥርጊያ መንገድ ለመሥራት በግሬደር እና ሌሎችም ከባድ የሥራ መሣሪያዎች በሚካሄደው ቁፋሮ የቅዱሳን
አባቶች ዐፅም እየታረሰና እየፈለሰ መሆኑ የገዳሙን መነኮሳትና መናንያን ከፍተኛ ሐዘንና ጭንቀት ላይ ጥሏቸዋል፡፡
የማኅበረ መነኮሳቱ ደብዳቤ ጨምሮ እንደሚያብራራው የዛሬማ ወንዝ ግድብ ሲቆም በውኃ ሙላቱ ሳቢያ ከሚጠፉት የገዳሙ ወሳኝ ይዞታዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-
1/ ልዩ ስሙ አባ ነፃ የተባለ የብዙ ቅዱሳን ዐፅም በክብር የፈለሰበትና የረገፈበት፣ ብዙ መነኮሳት እና መናንያን የሚቀመጡበት (የሕርመት/ተዐቅቦ ቦታ) የጻድቁ አቡነ ተስፋ ሐዋርያት ቤተ ክርስቲያንና መቃብር እንዲሁምየሙዝ ቋርፍ በከፍተኛ ደረጃ የሚዘጋጅበት እጅግ ሰፊ የሆነ የአትክልት ሥፍራ፤ 2/ በመዘጋ የሚገኙት ሞፈር ቤቶች/በገዳሙ ውስጥ እህል ስለማይበላ የዓመት ቀለብ የሆነ ቋርፍ የሚዘጋጅበት የአትክልት ስፍራ/፤ 3/ በመዘጋ የገዳሙ መነኮሳት እህል የሚቀምሱበት ቤት፤<?xml:namespace prefix = o ns = "urn:schemas-microsoft-com:office:office" />4/ ጥንታው
Comment